Email:
Subject:
Message:
August 2020
SMTWTFS
1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031

      መቅደላ ኮንስትራክሽን

   ስንገነባ ዛሬን ሳይሆን ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ በማድረግ ነው!!

መቅደላ ኮንስትራክሽን በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት ተመዝግቦ የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ኩባንያው ጋፋት ኢንዶውመንት የበጎ አድራጎት ስራውን ለማከናወንና  እና በአማራ ክልል የገበያ ክፍተት የሚስተዋልባቸውን የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሙላት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ሃብት ለማመንጨት ካቋቋማቸው አራት ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ኩባንያው በክልሉ ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን በዘርፉ የክልሉን መንግስት ጥረት ለመደገፍ በ2004 ዓ.ም የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡

መቅደላ ኮንስትራክሽን  በአማራ ክልል ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ በሚካሄዱ የመንገድ፤ የድልድይ እና የህንፃ ግንባታ ስራዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አዋጭነት ያለው እና የአካባቢ ደህንነትን ባገናዘበ ሁኔታ በመገንባት ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ የማድረግ ተልዕኮ እና እ.ኤ.አ. በ2030 በመንገድ፣ በድልድይ እና በህንፃ ግንባታ ዘርፍ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ አርኪና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ መሆንን ረዕይው አድርጎ ይህን ለማሳካት እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ይህነ ለማሳካትም የሚከተሉትን እሴቶች የእለት ተእለት የስራ መመሪያው አድርጎ የሚንቀሳቀስ ኩባንያ ሲሆን እነዚህም፡-

  • ተልዕኳችንና ራዕያችንን ለማሣካት በቁርጠኝነት እንሰራለን !
  • በውጤት መለካትን እናምናለን !
  • በጊዜና በጥራት መፈፀም መለያችን ነው !
  • የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብን አጥብቀን እንታገላለን !
  • ቁጠባን ባህላችን እንደርጋለን !
  • ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ ዕድል መፍጠር የስራችን አንዱ አካል እናደርጋለን !
  • ታማኝነት፤ ሚዛናዊነትና ቅንነት ያለው አገልግሎት መስጠት መለያችን እናደርጋለን !
  • የአካባቢ ደህንነትን እንጠብቃለን !

የሚሉት ናቸው፡፡

ኩባንያው ታማኝነት፣ጥራትና ቅልጥፍናን መርሁ በማድረግ በድልድይ፣በመንገድና በህንጻ ግንባታ ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን የማከራየት አገልግሎትም ይሰጣል፡፡

በዚህ መርህ በመመራትም መቅደላ ኮንስትራክሽን ከተቋቋመ ጀምሮ ባለፉት ስድስት አመታት 23 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድን ጨምሮ ከ 40 የሚበልጡ የግንባታ ፕሮጀክቶችን አከናውኗል፡፡እነዚህም እያንዳንዳቸው የተቀመጠላቸውን የጥራት መስፈርት አሟልተው በመገንባታቸው ኩባንያው አንድም ለደንበኞቹ እርካታን መፍጠር ችሏል፤ሌላም ለራሱ ምስጋናና ተመራጭነትን አግኝቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር ኩባንያው በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ባለቤት መሆኑ ፣ በዘርፉ የሚገኙ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም  አንዱ የኩባንያው የስራ ባህል ማድረጉ ብሎም ኩባንያው በተለይ በአማራ ክልል ለስራ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችና አከባቢዎች ጭምር ገብቶ በመገንባት የክልሉን ልማት ከማገዝ ባሻገር የህዝብ አለኝታነቱን እያረጋገጠ የሚገኝ መሆኑም እንዲሁ፡፡

ይህን ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ብሎም በዘርፉ በከፍተኛ የግንባታ ፕሮጀክቶች በመሳተፍ ለክልሉ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የግንባታ ፍቃዱን ወደ ደረጃ ሶስት ጠቅላላ ተቋራጭነት አሳድጓል፡፡በዚህ ደረጃ ለሚካሄዱ የግንባታ ስራዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን የማሟላት ስራም አከናውኗል፡፡

ለአንድ ኮንትራክተር ስራዎችን በወቅቱና በጥራት ገንብቶ ማስረከብ ብቻ በቂ አይደለም፤ተጨማሪ እሴት ይጠበቅበታል፡፡በመሆኑም የመቅደላ ኮንስትራክሽን ፍላጎትም ከዚህ ይልቃል፡፡ለክልሉ እና ለደንበኞቹ ሃብት ብሎም ግብአት መሆንን አልሞ ይሰራል፡፡

በዚህም ለበርካቶች የስራ እድልን መፍጠር ችሏል፤ክልሉም በዘርፉ እያደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ የዘርፉን ልማት በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡

Mekdella Construction Plc is one amongst the four companies owned by Gafat Endowment, began its operation in 2012 GC. It is a licensed grade three general building contractor, specializing in the construction of buildings, bridges and Roads.

መቅደላ ኮንስትራክሽን በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት ተመዝግቦ የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ኩባንያው ጋፋት ኢንዶውመንት የበጎ አድራጎት ስራውን ለማከናወንና እና በአማራ ክልል የገበያ ክፍተት የሚስተዋልባቸውን የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሙላት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ሃብት ለማመንጨት ካቋቋማቸው አራት ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ኩባንያው በክልሉ ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን በዘርፉ የክልሉን መንግስት ጥረት ለመደገፍ በ2004 ዓ.ም የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡

መቅደላ ኮንስትራክሽን በአማራ ክልል ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ በሚካሄዱ የመንገድ፤ የድልድይ እና የህንፃ ግንባታ ስራዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አዋጭነት ያለው እና የአካባቢ ደህንነትን ባገናዘበ ሁኔታ በመገንባት ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ የማድረግ ተልዕኮ እና እ.ኤ.አ. በ2030 በመንገድ፣ በድልድይ እና በህንፃ ግንባታ ዘርፍ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ አርኪና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ መሆንን ረዕይው አድርጎ ይህን ለማሳካት እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

Link

Mekdella Construction Plc is one amongst the four companies owned by Gafat Endowment, began its operation in 2012 GC. It is a licensed grade three general building contractor, specializing in the construction of buildings, bridges and Roads.

Mekdella construction is currently one of the leaders in the Amhara region construction industry, noted for quality projects delivered on time and its pioneering application of advanced construction methodology.

009023
1
1
544
9023

1
change background color joomla